በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ በጋዜጠኝነት፤መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና የሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን በደል ምስክርነት ሰምቷል

በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ በጋዜጠኝነት፤መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና የሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን በደል ምስክርነት ሰምቷል

አባይ ሚዲያ ዜና

ጋሻው ገብሬ

በትላንትናው እለት በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሚስተር ክሪስ ስሚዝ በተገኙበት ስለ ሰሃራ በታች አገራት የጋዜጠኝነት መብት እና የሀይማኖት ነጻነት ላይ መንግስታት የሚይደርጉትን ጭቆና አስመልክቶ ምስከርነት ሰምቷል። አንድ ሰዓት የፈጀው ምስክርነትና የጥያቄና መልስ ወቅት አምስት ምስክሮች ቀርበው ቃላችውን የሰጡበት ነበር። ከነዚህ መካክል የአሜሪካ ድምጹ የአፍሪካ የዜና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ መንገሻ ይገኙበታል። የአቶ ንጉሴ ምስክርነት ያተኮረው ሩዋንዳ በተሰኘችው አገር የሆነው አሳዛኝ ሁኔታ ነበር። ከ2015 ዓም ጀምሮ ሩዋንዳ 400,000 ህዝብ የተፈናቀለባት አገሩንም ትቶ በታንዛኒያ ስደተኛ ካምፖች የሚገኝባት አገር ናት። ቡሩንዲ ከዓለም አገራት ደሃይቱ ናት።የየአገራቱ የጋዜጠነት ነጻነት መለኪያ ከ180 አገራት መካከል 159 ንኛ ሆና የተመደበች ናት። አንድ መቶ የሚሆኑ ጋዜጠኖች የተሰደዱባትም አገር ናት።ጋዜጠኞች በፍርሀት ተሸማውቀው እንዳይናገሩ ተሸብበው ያሉባት አገር መሆንዋን የአቶ ንጉሴ ዘርዝረው አስረድተዋል። አቶ ንጉሴ ምስክርነታቸው በሩዋንዳ ላይ ያተኮረ ቢሆንም በጥያቄና መልሱ ወቅት ሲያስረዱ ባገራችን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያም ልክ እንደ ቡሩንዲ ጋዜጠኖች መከራ እንደሚያዩ አስረድተዋል። ኢትዮጵያም ብዙ ጋዜጠኖች እንደተሰደዱ በእስርም እንደተንገላቱ አስረድተዋል።በቅርቡ ከእስር ተፈትቶ አሜሪካ የሚገኘውን ጋዜጠኛ አቶ እስክንድረ ነጋን እንደማሰርጃ አቅርበዋል። እንደ አቶ ንጉሴ ምስክርነት የአሜርካ ድምጽ የቡሩንዲው ሁኔታ የገጠመው ችግር እንደምሳሌ ሲሆን ችግሩ ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት አጠቃላይ ነው። የዜና ማግኘት ነጻነት፤የዴሞክራሲ መብት እና የሰባዊ መብቶች እንደተረገጡ ናቸው በማለት አቶ ንጉሴ መስክረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአማርኛ እና የኦሮምኛ ፕሮግራሞችን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይተላለፉ አዳጋች የአየር ሞገድ በመልቀቅ ዜና እንዳይተላለፍ እንደሚያግድም ተናግረዋል። የአሜሪካ ምክር ቤት ለአሜሪካ ድምጽ የሚያደርገውን ቀጣይ ድጋፍም አመስግነው ምስክርነታቸው አጠቃለዋል። ከአቶ ንጉሴ ቀጥሎ የመሰከሩት ጆን ፔንደርጋስት የተባሉ የሰባዊ መብት ተከራካሪ፤ደራሲና የቀድሞ የአሜሪካ ጸጥታ ካውንል የአፍሪካ ዳይሬክተር ናቸው። ጆን ፔንደርጋስት ከመንግስት ተጽኖ ውጭ በነጻነት መንቀሳቀስ የሚገባቸው ህዝባዊ ድርጅቶች( civil society) ባለ አቅማቸው ራስን የመግለጽ ነጻነታቸው እና የመደራጀት መብቶቻቸው ተከብረው ከሳሀራ በታች ባሉ አገራት መስራት አልቻሉም ብለዋል።የመገናኛ ተቋማት አስቸጋሪነት ባላቸው ህግጋት ተሸብበዋል።በዚህ መንገድ ጨቋኞች ህዝቡን አፍነው ያኖራሉ ብለዋል። By ጋሻው ገብሬ – May 10, 2018 5/10/2018 በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ በጋዜጠኝነት፤መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና የሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን በደል ምስክርነት ሰምቷል | አባይ ሚዲያ http://amharic.abbaymedia.info/archives/44160 2/3 ጆን ፔንደርጋስት እንዳሉት እነዚህን መታገዝ የሚገባቸውን ህዝባዊ ድርጅቶች መርዳት የሚቻለው በሁለት የተዛመዱ መንገዶች ነው።አንደኛ በሁሉም አቅጣጫ የማእቀብ መረብ መዘርጋት።ሁለተኛ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያዘዋውሩባቸውን መንገዶች ማገድ ናቸው።ሚስተር ጆን ፔንደርጋስት የአሜሪካ መንግስት እነዚህን መንገዶች መጠቀም ይችላል፤ጫና ለማድረግ ይረዱታል ባይም ናቸው። የጨቋኝ የመንግስታት ባለስልጣናት የግል ሀብት የሚያግበሰብሱት በሙስና ነው።ሙስናውን ለማካሄድ ህዝብን ማፈን አለባቸው።ይህ ነው ከሳሃራ በታች ባሉ አገራት የሚካሄደው ብለዋል።መሰረታዊ የነጻነት መብቶች ሰባዊ መብትም የተረገጠ በመሆኑ የነዳጅ ዘይት፤ወርቅ፤አልማዝ፤ኮባልት፤መዳብ፤የደን ሀብት እየተሸጠ ጨቋኞች የግል ኪስ ይገባል። ይህን ወንጀል ለማገድ አሜሪካ እና የዓለም አቀፉ ህብረተሰብ የተጠቀሱትን የእቀባ መንገዶች መጠቀም ይችላሉ ባይ ናቸው።ወንጀለኞችን ብቻ ሳይሆን የሚተባበሯቸውን የግድ ተቋማትም በህግ መጠየቅ ያስችላል ብለዋል።የአሜሪካ ምክር ቤት እነዚህ ጫና ማድረጊያ መንገዶችን ተጠቅሞ የመንግስት ፖሊሲን ሊቀይስ ይቻለዋል በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል። ቀጥሎ ምስክርነት የሰጡት ሚስ ናንይቴ ታላኒ ናቸው። ታላኒ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸው፤ከስር ወጥተው አሜሪካ በጥገኝነት ያሉ ጋዜጠኛ ናቸው።ቀድሞ ባገራቸው ዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋዜጠኛነት ለብዙ ዓመታት ሰርተዋል።በምንስክርነነቸው የኮንጎ መንግስት የጋዜጠንነትን ነጻነትን በህግ አፍኖ የሚረግጥ ነው ብለው ተናግረዋል። አራተኛው ምስክር ሚስተር ስቲቭን ሃሪስ የስነ ምግባርና የሀይማኖት ተከራካሪ( The Ethics and Religious Liberty Commission Southern Baptist Convention) ሲሆኑ እሳቸውም የአሜሪካ ምክር ቤት የአፍሪካ ኑኡስ ኮሚቴ በአፍሪካ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል ማዳመጡንና ድምጽ አልባ ለሆኑት ህዝቦች ማገዙን አድንቀዋል። የሚስተር ስቲቭን ሃሪስ ድርጀት 15.2 ሚሊዮን አባላት የሚገኘባቸውን 46,000 ቤተ ክርስቲያኖችን የሚወክል ማህበር ነው።ሚስተር ስቲቭን ሃሪስ በሱዳን የሚገኙት አብያተ ክርስቲካናት ላይ የኦማር አል ባሺር መንግስት ስለዳረገው ጥቃት ተናግረዋል። አምስተኛው ምስክር ሚስተር ኤመርሰን ስካይስ የአፍሪካ አትራፊ ያለሆኑ ድረጀቶች ዓለም አቀፍ ማእከል የህግ አማካሪ ናቸው።(International Center for Not-for-Profit Law) እሳቸውም መንግስታት በህግ ደንግገው የሚያደርሱትን በደል አንስተዋል። ሚስተር ኤመርሰን ስካይስ በሩዋንዳ፤ደቡብ ሱዳን እና በኮንጎ ዴሞርክራቲክ ሪፑብሊክ ጭምሮም በአገራችን ኢትዮጵያ ህወሃት መሩ መንግስት መንግስታዊ ያልሆኑ ድረጅቶችን ለማፈን ያወጣውን “ሽብርተኛን ለመዋጋት” ብሎ የሰየመውን የጭቆና አዋጅ ተቅሰው ኮንነዋል። ሙሉ ምስክርነቱ በታች ካለው መስፈንጠርያ ይገኛል https://foreignaffairs.house.gov/hearing/subcommittee-hearing-protecting-civil-society-faith-based-actors-and-politicalspeech-in-sub-saharan-africa/ 5/10/2018 በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚ