ኢትዮጵያኖች የጀመሩትን ዘመቻ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ

ኢትዮጵያኖች የጀመሩትን ዘመቻ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ!

ባለፈው ወር ያለፈውን ኤቻር 128 ን ተከትሎ አሁን የተጀመረው ሴአር 168 ይጠናከር ዘንድ የኢትዮጵያ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ሰብሳቢ ዲ ዮሴፍ አሳሰቡ። በተለይም በየስቴቱ ያልፈረሙ ሴነተሮች ይፈርሙ ዘንድ በቀላሉ የሚያሳይ ዳታ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።


ኢትዮጵያኖች በቀላሉ ከተማቸውን በካርታው ላይ በማየት ተወካዩ መፈረምና አለመፈረሙን ማወቅ ይቻላል ብለዋል። በዚህም ቀይ ከሆነ ሙሉ በሙሉ መደወል እና በመፃፍ ግዴታችንን መወጣት አለብን። ቢጫ ከሆነ አንደኛው ብቻ ፈርሞል ማለት ሲሆን የተቀረውን እንዲፈርም ዘመቻ ማድረግ ይኖርብናል ። አርንጎዴ ከሆነ ደግሞ ሁለቱም ፈርመዋል ማለት ነው ሲሉ በዝርዝር ገልፀዋል።