ኮሎራዶ ኢትዮጵያውያን ለተከበሩ ማይክ ኮፍመን የተሳካ የእራት ግብዣ አደረጉ

ኮሎራዶ ኢትዮጵያውያን ለተከበሩ ማይክ ኮፍመን የተሳካ የእራት ግብዣ አደረጉ

ታሪካዊ ነበር ሲሉ የገለፁት አዘጋጆቹ ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ ኢትዮጵያኖችና ኣሜሪካኖች ተገኝተው እንደነበር እና ከተጠበቀው በላይ ህዝብ በመምጣቱ የአዳራሽ ጥበት እና የእራት ምግብ ማነስ ችግሮች እንደነበሩ ቢገልፁም የተባሉት ችግሮች ወነበሮችን በማስገባትና ተጨማሪ ምግቦችን በማቅረብ መቀረፋቸውን ተናግረዋል። በእለቱ ከተለያዩ ግዛቶችህ የተላኩ የእናመሰግናለን መልክቶች ለኮንግረስማን ኮፍመን ቀርበዋል በተለይም ዶር አርአያ አምሳሉ የአድቮከሲ ኔትወርክ ሰብሳቢ በቦታው ለመገኘት ያለመቻላቸውን በመግለፅ ዲ ዮሴፍ በአለቱ በቪዲዮ የተላለፈውን መለክት ለኮንግረስማን ኮፍመን አሳይተዋል። ኮፍመን በጣም እንደተደሰቱ እና ይህ ትግል እንዳላለቀም ተናግረዋል። አቶ ኦባንግ ሜቶም እንዲሁ መልክት የላኩ ሲሆን በረካታ የአሜሪካ ግዛቶች በቪዲዮ የእናመሰግናለን መልክቶች ቀርበውላቸዋል።

ለተወካዩ የኢትዮጵያውያን ብቻ መገለጫ የሆነውን የፊደል ገበታ በስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን በተጨማሪም የጥሩ ዜጋ የሰበአዊ መብት አሸናፊ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።

ለምርጫ ቅስቀሳም የገንዘብ መዋጮ ተደርጎላቸዋል። ኮፍመን ከፊታችን የሚጠብቀንን የኤስ አር 168 ትግል ማፍጠን አለብንም ብለዋል። ይህ የተደረገልኝን መልካም አቀባበልን እጅግ አድርጌ አመስግማለሁ ኢትዮጵያኖች ኩሩና ሀገር ወዳድ ናችሁ አሜሪካያኖች ይወዶችሆል ለምታደርጉት ማናቸውም እንቅስቃሴ ከጎናችሁ ነኝ ሲሉ ለተሰብሳቢ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። የተለያዩ የእምነት ተቆማትም በቦታው ተገኝተው ያመሰገኑ ሲሆን የውጩ ሲኖዶስም ደብዳቤ ተነቦል።