የአባይን ስምምነት እና ፍትሃዊ ድርድርን በተመለከተ ኢትዮጵያን የሚጠቅም አዲስ ሪዞሊሽን ይወጣ ዘንድ ንግግር መጀመራቸውን ዲ ዮሴፍ ተፈሪ ገልፀዋል

የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል፣ አድቮከሲ ኔትወርክ፣ የዲሲ ግብረሃይል፣ ፅናት፣ መደመር በተግባር፣የትውልድ ድልድይ፣ we aspired የወጣቶች የሶሻል ሚዲያ፣ ኢትዮጵያውያን በካናዳ እና ታዋቂ ኢትዮጵያን አሜሪካውያን በቨርጅኒያ የሚኖሩ ግለሰቦችና እንዲሁም የአፍሪካን አሜሪካውያን የጥቁሮች ስብስብ ተወካዮች የተሳተፉበት ታላቅ ስብሰባ ማክሰኞ ኤፕሪል 8፣ 2020 ቨርቾል የኦላይን ስብሰባ በታላቁ የአባይ ግድብ ስምምነትና ዘመቻ ዙርያ ተወያይተዋል።  

የአድቮከሲ ኔትወርክ ሰብሳቢ ዶ/ር አርአያ አምሳሉ አሁን በአለማችን የተከሰተው COVID19 ውረርሽኝ የጀመርነውን ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ፍትሃዊ የሆነ መብቷን ትጠቀም ዘንድ የፍትሃዊነት ዘመቻችን ውረርሽኙ ሊያስተጎጉለን አይገባም። ይህ የፍትሃዊነት ጥያቄ ለትውልድ የሚተላለፍ መሆኑን በመናገር የተጀመረው ስራ በቤት ውስጥ ሆነን የምንሰራው ስለሆነ አጥብቀን እንድሄድበት አደራ ብለዋል።

የዘመቻው አስተባባሪ የሆኑት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካወንስል ሰብሳቢ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ይህንን የመጣብንን መከራ ለማለፍ መንግስት ያውጣቸውን Social Distance guide እና ሌሎች ከባለሙያዎች የሚሰጠውን ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን በማድረግ ራሳችንን ከ COVID19 መጠበቅ እንዳለብን ተናግረዋል። የተጀመረው ዘመቻችን አሜሪካ በአባይ ግድብ ላይ እጇን ታነሳ እና ፍትሃዊ ስምምነት በታችኛው ተፋሰስ ሃጋራት እንዲኖር የምናደርገው ግፊት የቀጠለ መሆኑን እና ከአሜሪካ መንግስት ጋር ጫናውን እንዲያነሱ የምናደርገው ውይይት ውጤት እያስገኘ መሆኑን እና በተለይም በኦንላይን የጀመርነው ፊርማ ከ125ሺ በላይ መድረሱ አስታውቀው አሁንም ያልፈረሙ ኢትዮጵያኖች ይህንን https://www.change.org/EthiopianAmerican የተባለውን የተቃውሞ ድምፅ ፊርማ  እንዲፈርሙ አሳስበዋል። 

ፊርማው ኢትዮጵያኖችን ብቻ ሳይሆን የሚመለከተው የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑትን ከጎረቤት እስከ ስራ ባልደረባን ያካትታልም ብለዋል። በተለይም በአሜሪካ ትልቅ ኔትወርክ ያለው የጥቁሮችን ጥቅም የሚያስከብረውና በአሜሪካ ጫና ፈጣሪ የሆነው አስተባባሪ  NAACP African American Black Caucus ይህንን ዘመቻ ኢንዶርስ ማድረጋቸው ለኢትዮጵያኖች ታላቅ ድል መሆኑን ገልፀዋል። ይህን ተከትሎ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወስጥ የሲቪክ ካወንስሉ ከአሜሪካን ምክርቤት ባለስልጣናት እና The African American Black Caucus Rep ጋር በመሆን የአባይን ስምምነት እና ፍትሃዊ ድርድርን በተመለከተ ኢትዮጵያን የሚጠቅም አዲስ ሪዞሊሽን ይወጣ ዘንድ ንግግር መጀመራቸውን ለተሰብሳቢው ዲ ዮሴፍ ተፈሪ ገልፀዋል። 

በቨርጅኒያ ነዋሪ የሆኑት ዳኛ ፍሬሂዎት ሳሙኤል በበኩላቸው ይህንን የሚመጣውን ሪዞሊሽን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በየሚኖሩበት ከተማ ያላቸውን ተወካዮች ስፖንሰር እንዲያደርጉት ትብብር ማድረግ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። የሲቪክ ካውንስሉ የፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት ኢንጅነር አይንሸት ገላጋይ በበኩላቸው በHRes128 ያገኘነውን ታክቲክ እና ድል በመጠቀም ተመሳሳይ ስራ በመስራት ኢትዮጵያውያን በአባይ ግድብ ላይ ፍትሃዊ የሆነ የመጠቀም መብታችንን ማስከበርና ከተደራዳሪዎች ጎን በመቆም ታሪክ መስራት እንዳለብን አሳስበዋል። 

ኢትዮጵያ ይህን የአባይ የፍትሃዊነት ጥያቄ ማቅረቧ ትክክለኛና እኛ ጥቁር አሜሪካውያኖች የምንደግፈው መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁም ሲሉ የሳንሆዜ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ አረጋግጠዋል። በመጨረሻም ይህንን ዘመቻ ለመጀመር  የሚያስችሉ ዶክሜንቶች ተዘጋጅተው ያለቁ መሆናቸውንና ይህ ዶክሜንት ለፅናት የኦንላይን ዘመቻ አስተባባሪዎች መላኩን ዶ/ር አርኣያ አምሳሉ ገልፅው፣ ለዚህም በቀላል መንገድ ሁሉም ኢትዮጵያኖች በየከተማቸው ያሉ ተወካዮቻቸውን የሚያገኙበት ዘዴ የተመቻቸ እና ለዛም የሚላክ ደብዳቤ ተረቆ ያለ በመሆኑ ይህንን ለማግኘት የሚፈልግ በውስጥ መስመር ወይም ማናቸውንም የዲሲ ግብረሃይል፣ ፅናት፣ መደመር በተግባርና የትውልድ ድልድይ አባላትን መጠየቅ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። በተለይም በፌስቡክ ገፃችን ፈጣን ምላሽ እንደምንሰጥ ወይም ከማናቸውም የስቴት የአሜሪካን ሲቪክ ካወንስል አባላት ዶክሜንቱ እንደሚገኝ በመግለፅ ስብሰባውን ዘግተዋል።