የተባበሩት መንግስታት የግብፅ መኪና ሆኖ ከማገልገል እንዲቆጠብ ረቂቅ ህግ መውጣት አለበት ሲሉ ጀሲ ጃክሰን ተናግሩ

ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በአሜሪካን ሀገር የታላቁን የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ፍትሃዊ የመጠቀም መብቶን ካለምንም የውጭ እና የግብፅ ጫና ስራዋን ታካሂድ ዘንድ የሚደረገው ዘመቻ መጠናከሩን የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ አስታወቁ።

ይህን ተከትሎ በአሜሪካን ሀገር የህግ አወጪ አካላትን እና የፖሊሲ ጫና ፈጣሪ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ጎን እንዲሆኑ የሚደረገው ዲፕሎማሳዊ ዘመቻ መጠናከሩን እና ተጨማሪ ኢንዶርስመንት ከታላቁና ታዋቂው ጀሲ ጃክሰን ማግኘታቸውን ገልፀዋል። በዚህም መሰረት ታዋቂው የአሜሪካው የሰበአዊ መብት ተሞጋች ድርጅት መስራችና ፕሬዝዳንት Jesse Jackson American civil rights activist ለተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ የመጠቀም መብትን ዘመቻ በማጠናከር ደብዳቤ አስገብተዋል። ይህም በአሜሪካን ሀገር የጥቁር አሜሪካውያን ሲደግፉት ሁለተኛው ነው።

በዚህም መሰረት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ የሚገኙ የአፍሪካን አሜሪካውያን የጥቁር ስብስቦች በኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ላይ የሚደረግ ማናቸውንም አላግባብ ጫናዎች ከኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ዲያስፖራ ጎን በመሆን ተቃሞቸውን አስታውቀዋል። የተከበሩ ጀሲ ጃክሰን ለአሜሪካ ምክርቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊና የብላክ ካከስ ሃላፊ እና ለተከበሩ ካውንስልውመን ኬረን ባስ በፃፉት ደብዳቤ የተባበሩት መንግስታት የግብፅ መኪና ሆኖ ከማገልገል እንዲቆጠብ ረቂቅ ህግ መውጣት አለበት ሲሉ ጠንከር ባለ ደብዳቤ ቅሬታቸውን አስገብተዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ ከአባይ ተጠቃሚ ሆናም አታውቅም ሲሉ ተናግረዋል። ግብፅ ያልተገባ አቀራረብና አቆሞን ካላስተካከለች አሜሪካ የጥቁር ሀገራትን ሉአላዊነት የማስከበር ግዴታ አለባት ብለን እናምናለን። ሀገራት ፍትሃዊና ካለምንም ጫና ስምምነት ማድረግ ይገባቸዋል በተለይም ኢትዮጵያ ካለችበት ድህነት የምተወጣበት ተፈጥሮዊ ሀብቶን መጠቀም ይገባታል ብለን እናምናለን ሲሉ ለምክርቤቱ ተወካይ ኬረን ባስ እና ለተባበሩት መንግስታት አስታውቀዋል።

በአሜሪካን ምክርቤት ብቸኛው ለአለም የጥቁር ሀገራት ተቆርቆሪ እና ተወካያችን የሆነው በአሜሪካን ምክርቤት Black Caucus ይህንን ጉዳይ አትኩሮት በመስጠት በታሪክ የተለመደውን ድጋፍ ለኢትዮጵያኖች መስጠት ይኖርበታል:: ስለዚህ አስቸኮይ ረቂቅ ህግ እንዲወጣ የተከበሩ ጀሲ ሳክሰን ጠይቀዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ከNACCP ጋር በመሆን ረቂቅ ህግ ድራፍት እየተዘጋጀ መሆኑን ባለፈው ጊዜ ማስታወቃችን ይታወቃል