ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እንዳትጠቀም ተፅዕኖ ለማድረግ የሚሰሩ ሀገራትና ተቋማት እጃቸውን ሊሰበስቡ እንደሚገባ ተገለፀ።

ፖለቲካ የሚቀየርና የሚሄድ ነው። ሀገር ግን ለዘላለም የሚኖር ነው ስለዚህ እባካችሁ መስከረም በሆላ መንግስት የለም እያላችሁ ግብፅን አታበረታቱ ሲሉ የኢትዮጵያ ሲቪክ ካውንስል ፕሬዝዳንት ዲ #ዮሴፍ_ተፈሪ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ ተናገሩ።
ዛሬ #ከኢቲቪ ጋር የሲቪክ ካውንስሉ ፕሬዝዳንት ዲያቆን #ዮሴፍ ተፈሪ እና የፕሮጀክት ማናጀሩ ኢንጅነር #አይንሸት #ገላጋይ ባደረጉት የአባይ ግድብ ሂደትና ዘመቻ በውጭ ሀገር ምን ይመስላል በሚለው ላይ ሰፊ ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል። 
ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል በኮሎራዶ ተመስርቶ በመላው አሜሪካ የሚገኙትን ዲያስፖራ በሰበአዊ መብት መከበር እና ዲፕሎማሲ ስራ የተሰማራ ከመሆኑ ባሻገር በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከኢትዮጵያውያን አድቮከሲ ኔትወርክ ጋር በመዋሃድ ሁለት አይነት ስልቶችን ይዞ የሚንቀስቀስ ትርፋማ ያልሆነ ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም ካውንስሉ ና አድቮከሲ ኔትወርኩ ኢትዮጵያውያን በታሪክ የማይረሱትን HRes128 እንዲያልፍ ያላሳለሰ ጥረት ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመሆን የሰራ ድርጅት ነው ሲሉ ስለ ድርጅታቸው ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰአት አባይን ከሰበአዊነት ሳይሆን ከሉአላዊነት  አንፃር በማየታችን ሁሉም ዲያስፖራ የፖለቲካ ልዩነቱን በመተው ሀገሪቱን በማስተዳደር እና በመደራደር ላይ ካለው የአቢይ መንግስት ጎን በመቆም ፍትሃዊ አጠቃቀም እንዲኖር በመፈለግ አባይ የኔ ነው ኢትዮጵያ ፍትሃዊ አጠቃቀምን እንጂ ግብፅን ለመጉዳት አላማም ፍላጎትም የላትም በሚል እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል። 
በዚህም  የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ጀምሮት የነበረውን ጫና በአስቸኳይ እንዲያቆም  በኦንላይን ፊርማ ከ 140ሺ በላይ በማሰባሰብ እና ቀጥታ ለግምዣ ቤት ሃላፊው ደብዳቤ በመፃፍ ጫናቸውን እንዲያቆሙ እስከ ማድረግ ደርሰናል። በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ የጥቁር አሜሪካውያን ጫና ፈጣሪ የሆነውን NACCP ኢትዮጵያን ደግፎ ፊርማውን እንዲፈርም ከማስደረግ ባሻገር አዲስ ረቂቀ ህግ በአሜሪካን ምክር ቤት እንዲወጣ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር እንቅስቃሴ ጀምረናል ብለዋል። ይህ የሚያሳየው በውጪ ሃገራት ዲያስፖራው በጋራ የፖለቲካ ልዩነቱን ወደጎን አድርጎ ሲሰራ በህግ አውጪ አካላትና የአሜሪካ መንግስት አስተዳደር ላይ ጫና መፍጠር እንደሚችል ያረጋገጠልን ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ቃለምልልስ ያዳምጡ።

#etv ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እንዳትጠቀም ተፅዕኖ ለማድረግ የሚሰሩ ሀገራትና ተቋማት እጃቸውን ሊሰበስቡ እንደሚገባ ተገለፀ።

Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Monday, May 25, 2020