የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን የህልውና ጉዳይ ነው። ኢንጅነር አይንሸት ገላጋይ EACC

ኢንጅነር አይንሸት ገላጋይ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል የፕሮጀክት እና ፕላን ሃላፊ ከፅናት የሶሻል ሚዲያ ግሩፕ ጋር ባደረጉት ውይይት ገለፁ::

ግብፆች በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይና ዲፕሎማሲ የለም: ይሁን እንጂ የዲያስፖራውና የተደራዳሪው ቡድን የተናበበ በሚመስል መልኩ የተቀናጀ ስራ እና ዲፕሎማሳዊ ዘመቻ በመጀመር ይህ ጫና እንዲከሽፍ እና ግብፅ ወደትክክለኛ ድርድር እንድትመጣ የሚያስኬድ መንገድ ተጀምሮል::

ይህም በውጪም በውስጥም የኢትጵያውያን የጋራ ጥረት ነው። ኢትዮጵያ ማንንም ሀገር የመጉዳት አላማ የላትም:: በታሪክ ኢትዮጵያ የሀገራት የመልካም የትብብር ዲፕሎማሲ እንዲኖር ግንባር ቀደም መሪ ነች ስለዚህ አሁንም ቢሆን ምንም አይነት የጦርነት ነጋሪት ሳይሆን የጠረጴዛ ውይይት ብቻ ነው ለተፋሰስ ሀገራት መፍትሄው ሲሉ አብራርተዋል

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3253105094711847&id=2335571296685530