ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ115 አመት በላይ የዘለቀ ወዳጅነት አላቸው። ይህን ለማደፍረስ የግብፅ ያልተገባና ፍትሃዊ ያልሆነ ራስወዳድነትን አሜሪካ መደገፉ ፍትሃዊ አይደለም።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ115 አመት በላይ የዘለቀ ወዳጅነት አላቸው። ይህን ለማደፍረስ የግብፅ ያልተገባና ፍትሃዊ ያልሆነ ራስወዳድነትን መደገፉ ፍትሃዊ አይደለም።

የኢትዮ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ለተከበሩ ሮበርት ኦ ብርያን ለአሜሪካን ፕሬዝዳንት የብሄራዊ ደህነንት አማካሪ ዴሬክተር በድብዳቤ ቅሬታውን ገለፀ። ግብፅ ሆን ብላ በምታውሰበስብበት በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ በንፁህና ፍትሃዊ የሆነ ክፍፍል እንዲኖር ያላሳለሰ፣ ወቅቱ የሚጠይቀውም የመልካም ዲፕሎማሲ ሂደት እና ድርድር እያደረገች ነው። ይሁን እንጂ ግብፅ በጎንዮሽ ለታዛቢነት የተቀመጠችውን አሜሪካን መጠቀሚያ እያደረገች ነው።

ታሪካዊ ወዳጅነታችን አደጋ ውስጥ መግባት ስለሌበት ሁሉም ሀገራት ወደ ሰለጠነ ፍትሃዊና ገለልተኛ በሆነ መልኩ በድርድር መፍታት ይኖርባቸዋል ስንል ማሳሰብ እንወዳለን ሲል ዛሬ ለብሄራዊው የደህንነት ምክርቤት ዴሬክተር እና  ለፕሬዝድነቱ አማካሪ ባስገባው ደብዳቤ አስታውቋል።

ሰሞኑን የአሜሪካ የድህንነት መስሪያ ቤት ያወጣውን ቲዊት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።