ከአሜሪካን ምክርቤት የወታደራዊ ክፍል ንኡስ ኮሚቴ ሃላፊ የኮሎራዶው ኮንግረስማን ጀይሰን ክሮው አባይ ለኢትዮጵያ የሉአላዊነት ጥያቄ ነው ሲሉ ተናገሩ

ተጨማሪ ድጋፍ ከአሜሪካን ምክርቤት የወታደራዊ ክፍል ንኡስ ኮሚቴ ሃላፊ የኮሎራዶው ኮንግረስማን ጀይሰን ክሮውአባይ ለኢትዮጵያ የሉአላዊነት ጥያቄ ነው ሲሉ ተናገሩ!!
የኮሎራዶው ኮንግረስማን ጀይሰን ክሮው በአሜሪካን ምክርቤት ፍሎር ላይ ቀርበው የአባይ ጉዳይ ለኢትዮጵያውያን የህልውና እና ከድህነት መውጫቸው ነው። ኢትዮጵያ በድርቅና በድህነት ስትሰቃይ የነበረች ሀገር እንደመሆኗ ይህ ለህዝባቸውና ለአካባቢው ከተፈጥሯዊ ቀውስ መውጫቸው ነው።

https://www.congress.gov/congressional-record/2020/6/26/extensions-of-remarks-section/article/e582-3?s=1&r=1

በመሆኑም የዚህ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ለሁሉም የተፋሰስ ሀገራት  ፍትሃዊ ክፍፍልና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ነው። ስለሆነም ሀገራቱ የራሳቸውን ችግር  በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ የዩናይትድ ስቴት መንግስት የመፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ አድሎአዊነት በማሳየት ችግሩን ማባባስ ተገቢ አይደለም። ስለዚህም ምክርቤቱ የአባይን ግድብ መሰረታዊ እውነት በማጤን ኢትዮጵያ የያዘችውን የድህነት መውጫ መንገዷን መደግፍ  አለብን ሲሉ ለምክርቤቱ ሰብሳቢ ጠንክር አድርገው ተናግረዋል።  Please click the link ለሙሉው ንግግር ።