የውጭ ጉዳዮች ሃላፊና የፕሬዝዳንቱ የውጭ አማካሪ ከሆኑት ከኮሎራዶው Sen. Cory Gardner ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደረገ።

#GERD #Ethiopia #EACC/EAN Colorado
ኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስልና አድቮከሲ ኔትወርክ ከዩናይትድ ስቴት ሴኔት የውጭ ጉዳዮች ሃላፊና የፕሬዝዳንቱ የውጭ አማካሪ ከሆኑት ከኮሎራዶው Sen. Cory Gardner ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አደረገ።
ስብሰባው ሁለት መሰረታዊ አጀንዳዎች የነበሩት ሲሆን እነሱም፣ የትራምፕ በአባይ ጣልቃ መግባትና አሁንም ያሉ ጫናዎች የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እየተጋፋት ስለመሆኑና፣ የውጭ መንግስታት የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር በመጠቀም እርስ በርስ እንድንባላ ለማድረግ በብሄር የተደራጁ ቡድኖችን በማሰባሰብ አለመረጋጋት ለመፍጠር በሚያደርጉት ሂደት ታዋቂውንና ለነፃነት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደረገውን አርቲስት ሃጫሉን_ሁንዴሳን ማስገደላቸው ኢትዮጵያ ተረጋግታ ለውጡን እንዳትቀጥል እያደረጉ ስለመሆናቸው በስፋት ተወያይቶባቸዋል። 
በውይይቱ አባይ በሚቀጥለው ሣምንት ሙሊቱን እንደሚጀምር እና አሜሪካ ኢትዮጵያ የድህነት መውጫ የሆነውን ሃብቷን ካለምንም መሰናክል ህዝቧን ወደስልጣኔ ማማና የብርሃን ዘመን ታሸጋግርና ትገባ ዘንድ ያላሳለሰ ድጋፍና ጥረት እንደሁልግዜው መደገፍ አለባት ሲሉ ዲ #ዮሴፍ_ተፈሪ ለሴነተሩ አሳስበዋል። አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ታሪካዊ የማይረሳ የተሳሰረ ወዳጅነት አለን ይህ ወዳጅነት በፖለቲካ መሪዎች መጥፋት የለበትም። እንደ ፓርቲ ሳይሆን እንደ ሀገር የአሜሪካ በኢትዮጵያ ያላት መልካም መርህ መለወጥ የለበትም ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዘር ፖለቲካን ምክንያት በማድረግ ለውጡ ያልተዋጠላቸው አካላት ኢትዮጵያ በእርስ በርስ ግጭት እንደ ሶሪያና ሊቢያ ሊያደርጓት የሚያስቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የውጭ ዜግነት ያላቸውና ራሳቸው በተደላደለ ኖሮ እየኖሩ በሌላ ሀገር ላይ ገብተው ግድያና አለመረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ ላይ መሆናቸውን አቶ አምሳሉ ካሳው ለኒሁ የውጭ ጉዳይ ሰብሳቢ ሴንተር ኮሪ ተናግረዋል።  የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አለመረጋጋት ሆን ብለው የፈፀሙትን ተጠርጣሪዎች በመያዝ ሀገርን እያረጋጋ ቢሆንም ይህ ሂደት በተረጋጋ መልኩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሂደት እንዳይኖር እንዲሁም ትክክለኛውን የፍትህ ስርአት ለመጀመር ያስችል ዘንድ የውጭ አካላት በሃሰት የሚያራቡትን ዜና እና ጣልቃ የሚገቡትን ጉዳይ እንዲያቆሙ የዩናይትድ ስቴት ሴኔት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ጉዳዩን ይመለከተው ዘንድ አጥብቀው ጠይቀዋል።

 
እኒሁ የውጭ ጉዳይ ሰብሳቢ ሴኔተር ኮሪ ጋርደን ኢትዮጵያ የጀመረችውን ለውጥ እና እንዲሁም ዜጎች ከድህነት እና ከመሰረታዊ የኑሮ አስፈላጊ ከመብራት እጦት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት እጅግ እንደሚያደንቁ እና አስተዳደራቸው ይህንን እንደሚደግፍ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ሀገር ነች ማናቸውንም ተፈጥሯዊ ሀብቷን ተጠቅማ ከድህነት መውጣት አለባት። ይህ ሲሆን ደግሞ የዴሞክራሲና የአንድነት አብሮ በሰላም የመኖር እሴቶች በኢትዮጵያ ይረጋገጣሉ ብዪ አምናለሁ ብለዋል።ሴነተር ኮሪ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ የሚጠቅም ህግ ሴኔታቸው ባለፈው ጊዜ #Power_of_Africa_Bill አዘጋጅተው እንዳስፀደቁና እንደገና ይህንን ህግ አይተው ሁሉም ሀገራት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ እንደሚያመቻቹ ለተሰብሳቢዎቹ አረጋግጠዋል ። ከዛም ባሻገር ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም ሁሌም ቁርጠኛ ሀገር እንደመሆኗ መጠን የውጭ አካላት ይህንን ሰላም ከማደፍረስ እንዲቆጠቡ የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ሴንተር ኮሪ ጋርደን የትራምፕ አስተዳደርን፣ የውጭ ጉዳይ ሃላፊውን፣ የግምጃ ቤቱን ሃላፊና ሌሎችንም በሴኔተር ውስጥ ያሉ ሃላፊዎችን በሚቀጥሉት ሳምንታት በዚህ ጉዳይ ላይ እንደሚያነጋግሩና ውጤቱን እንደሚያሳውቁ ተናገረዋል።
ከኢትዮጵያ ጋር ታሪካዊ ወዳጅነታችን በዚህ የሚገታ እንዳልሆነ እና ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰሩ ከመናገራቸውም ባሻገር በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የተጀመረው ለውጥ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ሀገራት ሰላም ወሳኝ በመሆኑ መንግስታቸው የተጀመረው ለውጥ ችግሩን አልፎ በሁለት እግሩ ይቆም ዘንድ እንደሚሰሩ፣ ድጋፍ እንደሚያደርጉ እና በዘር ምክንያት የውጭ ሀገራትን ተሳትፎ ምን እንደሚመስል ከደህንነት ክፍሉ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል። በተለይም #የአሜሪካን_ዜግነት_ኖሯቸው በኢትዮጵያ የዘርና የሃይማኖት ግጭቶች የሚያነሳሱትን ቡድኖችና ግለሰቦች በተመለከተ #ከስቴት_ሴክሬታሪያቱ_ማይክ_ፒንፖ ጋር እንደሚወያዩ ቃል ገብተዋል። 
በስብሰባው  የCIADA አምባሳደር የቦርድ ዴሬክተርና የካውንስሉ የዝግጅትና ፕላን ሃላፊም #መርሃፅድ_አበበም ሴነተሩን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አድንቀዋል
በመጨረሻም ዲ ዮሴፍ ተፈሪ ሴኔተር ኮሪ ጋርደን #Sres168 ስፖንሰር በማድረግ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸው አቅርበዋል።