ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን ለሴክሬታሪ ኦፍ ስቴት Mike Pompeo ሰሞኑን በአክራሪ ብሄርተኛ አስተባባሪነት የገባላቸው ደብዳቤ ውድቅ እንዲሆን ዛሬ ባስገቡት ደብዳቤ ገለፁ።

ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ለአሜሪካ ባለስልጣን ለተከበሩ ሴክሬታሪ ኦፍ ስቴት Mike Pompeo ሰሞኑን በአክራሪ ብሄርተኛ አስተባባሪነት የገባላቸው ደብዳቤ ውድቅ እንዲሆን ዛሬ ባስገቡት ደብዳቤ ገለፁ።
ኦገስት 21 በሚኒሶታው ኮንግረስማን #ዲን_ፊሊፕስ እና የሰሞሌዋ ተወላጅ ኮንግረስውመን ኢላን ኦማር አስተባባሪነት ተፈርሞ ለአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሃላፊ ማይክ ፖምፒዎ የኢትዮጵያን ገፅታን የቀየረና የተዛባ ደብዳቤ መግባቱ ይታወሳል። 
ይህንን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዲያስፖራ  ይህ ደብዳቤ የተጀመረውን ለውጥ እና ሀገሪቱ ምን አይነት በዘር ግጭት መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሆነች፣ የጎሳ መሪዎች ዜጎችን እያስጨነቁ ስለመሆናቸው እና መንግስትም በመጨረሻ ቢሆን ይህንን #የህግ_የበላይነት የማስክበር ሂደት ላይ መጀመሩን እና እየሰራበት መሆኑን የሚክድ ሆኖ አግኝተውታል። 


በመሆኑም እነዚህ 20 ኮንግረስ በኦሮሞ አክራሪዎች ሎቢ ድርጅት አስተባባሪነት የተላከው ደብዳቤ ውድቅ ሆኖ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤቱ ያለውን እውነት እንዲያጣራ እና ኢትዮጵያ ከገባችበት የዘር ግጭት ትወጣ ዘንድ ህግና ስርአት እንዲኖር መንግስት የጀመረውን ሂደት የአሜሪካ መንግስት እንዲደግፍ #የኢትዮ_አሜሪካን_ሲቪክ ካውንስል በአስገባው ደብዳቤ ቅሬታውን አሳስቦል። 
በዚሁ ድብዳቤ የብሄርተኞች መሪዎች ጃዋርን ጨምሮ ለበርካታ ንፁሃን ሂወት መጥፋት ተጠያቂ ናቸው በተለይም የኦነግ ሸኔ ከፖለቲካ አጀንዳው ባሻገር የሃይማኖት አክራሪነትን እየሰበከ ነው እና ሊታሰብበት ይገባል ሲልም ለተከበሩ ማይክ ፖምፒዎ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሃላፊ የኢትዮ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ባለ 3 ገፅ ዝርዝር ደብዳቤውን ዛሬ አስገብተዋል።


ይህ ደብዳቤ ባለፈው  በ20 ኮንግረሶች ተፈርሞ የገባው ይዘት የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ካለማገናዘቡ ባሻገር ወገንተኝነት ስለታየበት የገባው ደብዳቤ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንዲሆንም ይጠይቃል። 

ደብዳቤውን ለማየት ይህን ይጫኑ

https://drive.google.com/file/d/1Ixabb1VQwSvpny3T8iY97lOJN5GzrnIq/view?usp=drivesd


ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሂደት ይጠናከር እና ይከበር ዘንድ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ  ይኖርባታል ሲል የተላከው ደብዳቤ ያትታል።https://drive.google.com/file/d/1Ixabb1VQwSvpny3T8iY97lOJN5GzrnIq/view?usp=drivesd