የአሜሪካኖችን የሴኔትና የኮንግረስ ውይይት በተሳካ ሁኔታ ከአፍሪካውያን ጋር ተካሄደ።

የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ለሁለት ቀናት Oct 10, and Oct 12, 2020 ያደረገው የአሜሪካኖችን የሴኔት እና የኮንግረስ ውይይት በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቆል። ይህ ፕሮግራም የአፍሪካ ፎረም በሚል ከአፍሪካ ሊደርሽፕ፣ ከኤርትራያን ኮሚውኒቲ እና ኢትዮጵያውያን ኮሚውኒቲ በኮሎራዶ ጋር በመተባበር የተካሄደ ፎረም ነበር።


በፎረሙ ላይ በሴኔት የውጪ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ሴኔተር ኮሪ ጋርድነር ከአፍሪካውያን ጋር ባደረጉት ውይይት በርካታ ነጥቦችን በማንሳት አፍሪካውያን በድጋሜ ይመርጡአቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ ለኮንግረስ ተወዳዳሪ የሆኑት ኮንግረስማን ጀይሰን ክሮው እና ስቲቭ ሃውስ በየበኩላቸው ለምን ለአፍሪካውያን የተሻሉ እንደሆነ ፕላናቸውን አስረድተዋል።
ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ዘንድ ይህን ሊንክ ይጫኑ