የተባበሩት መንግስታት የግብፅ መኪና ሆኖ ከማገልገል እንዲቆጠብ ረቂቅ ህግ መውጣት አለበት ሲሉ ጀሲ ጃክሰን ተናግሩ
ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በአሜሪካን ሀገር የታላቁን የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ፍትሃዊ የመጠቀም መብቶን ካለምንም የውጭ እና የግብፅ ጫና ስራዋን ታካሂድ ዘንድ የሚደረገው ዘመቻ መጠናከሩን የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ አስታወቁ። ይህን ተከትሎ በአሜሪካን ሀገር የህግ አወጪ አካላትን እና የፖሊሲ ጫና ፈጣሪ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ጎን እንዲሆኑ የሚደረገው ዲፕሎማሳዊ ዘመቻ መጠናከሩን እና